አፍሪካን የናፈቁ የታፈኑ ቅርሶች
አፍሪካን የናፈቁ የታፈኑ ቅርሶች Decolonize museum በሚለው መጽሃፏ የምትታወቀው ወጣቷ ደራሲ ሽምሪት ሊ እንዴት የእንግሊዝ ሙዚየሞች ከህንድ ከቤኒን እና ከናይጀሪያ ተዘርፈው በተወሰዱ እጅግ ውድ ቅርሶች እንደተሞሉ ብሎም በቅቡ በአራት ደቂቃ ዝርፊያ የተፈጸመበት የፓሪሱ ሉቨር ሙዚየም እንዴት ከግብጽ በተዘረፉ ቅርሶች እንደተሞላ በቁጭት ታስረዳለች፡፡ ሃገራት በተለይ በቅኝ ግዛት ዘመን የዘረፏቸውን ቅርሶች መመለስ አለባቸው ወይም በቀጣይ እጅግ ጠንካራ የፍትህ ስርአት ተዘርግቶ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ቅርሶች ወደ ቤታቸው መመለስ አለባቸው የሚል ጥብቅ መከራከሪያ ታቀርባለች፡፡